Friday, March 23, 2012

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት በወቅታዊ የገዳማት ሁኔታ ላይ መግለጫ ይሰጣል

 
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 13/2004 ዓ.ም፤ ማርች 22/2012 READ THIS IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በዋልድባ ገዳማት ክልልና ዙሪያ የሚካሄደው‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› ስለተፈጠረው ውዝግብ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና አካባቢ እንዲሁም በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ይዞታ በሆኑ ደኖች ስለደረሰው ቃጠሎ አደጋ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች - ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ዋና ሓላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ - በዋልድባ ገዳማት ጉዳይ ወደ ስፍራው አምርተው ከመንግሥት፣ ከአህጉረ ስብከት እና ከገዳሙ ተወካዮች ጋራ መነጋገራቸው በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እና በደጀ ሰላምም መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የሕዝብ ግንኙነቱ መመሪያው ምክትል ሓላፊው ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ እንዲሁም የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊው (መጋቤ ካህናቱ) ሊቀ ማእምራን ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም ከምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ጋራ በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ተጉዘው እንደ ነበር ተሰምቷል፡፡
በሰሞኑ የዝቋላ ገዳምና አካባቢው ቃጠሎ ደግሞ እሳቱ ከተነሣ ሦስት ቀናት በኋላ በገዳማት አስተዳደር መምሪያው ሓላፊ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ያሉበት ኮሚቴ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ውሎ እና አዳራቸውን በዚያው አድርገው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው የተመለሱት ትንት ረፋድ ላይ ነበር፡፡
ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሰማሩትን የሦስቱንም ቡድን ልኡካን ጉዞ ንቅናቄዎች አንድ የሚያደርጋቸው፡- ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ መንግሥት ዕቅዱን ለማሳመን የሚጥረውን ያህል ቤተ ክህነታችን እንደ ባለቤት አጀንዳውን የራስ በማድረግ ፈጣን ምላሽ አለመስጠቱ፣ አደጋውን ከሐቁ ለማሳነስ አንዳንዴም ጨርሶ ለማስተባበል የተሞከረበት መሆኑ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም ላይ አገርንም ቤተ ክርስቲያኒቱንም ሊጠቅም የሚችል አቋም ከመያዝ ይልቅ የመደራደር ዝንባሌ መታየቱ፤ ከዚህም አልፎ በቤተ ክርስቲያኒቷ ችግር የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የችግር አፈታትና የሕዝብ ግንኙነት አቅም ተፈትኖ ደካማ ሆኖ መገኘቱ ናቸው፡፡
እግዚኦ በሚያሰኝ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት ከሄዱበት ህልውናው በአደጋ ውስጥ ከሚገኝ ገዳምአበል ጠይቀውና ተቀብለው የመጡ አሳፋሪ ልኡካንም እንዳሉ ጥቆማው ደርሶናል፡፡
ለማንኛውም ‹ጨርሶ ከመቅረቱ መዘግየቱ ይመረጣል›ና የተባለውን ወቅታዊ መግለጫ እንጠብቃለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም፤ ማርች 21/2012/ READ IN PDF)፦ ስጋቱ ዛሬ አዳሩንከምሽቱ 300 ገደማ የቅዱሳን ከተማ በሚባለው ስፍራ ሲጤሱ የዋሉ የገመኑ (የተቃጠሉጉቶዎችና ግንዶች ምሽቱንእሳት መቀስቀሳቸው ተሰምቷል፡፡ የእሳቱ መጠን ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም÷ በየአቅጣጫውሁኔታውን በንቃት እየቃኙ በነበሩት መናንያን በተሰማው ደወል በገዳሙ አዳራሽ የነበረው ምእመን እንዲጠራ ተደርጎ፣በተራራው ላይ የመከላከሉን ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ሲያግዙ ከነበሩት የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኀይሎች ጋራየተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑ ተገልጾልናል፡፡

ንት ሌሊቱንና ዛሬ ውሎውን የቃጠሎው መዛመት ተግ ብሎ ከጋራው ግርጌ በኩል የሚጤሱ የጋሙ ጉቶዎች ጢስብቻ ነበር የሚታየው፡፡ ማምሻውን የተቀሰቀሰው እሳት በቃጠሎው ብዛት የገመኑት ግንዶችና ጉቶዎች የፈጠሩትን ፍሕምጨርሶ ለማጥፋት በአየር የሚረጨው ኬሚካል በእጅጉ አስፈላጊ እንደ ሆነ ያለማቋረጥ እየቀረበ ያለውን ጥያቄትክክለኛነት የሚያስረግጥ ነው፡፡ በመሆኑም በጎ አድራጊ አካላት ለዚህ ተፈጻሚነት እንዲተባበሩ ተጠይቋል፡፡
ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ የነፍስ ወከፍ የውኃ ርጭት ነው፡፡ ይሁንና ገዳሙ ከቀድሞም ባለበት የውኃ እጥረትናከፍሕሙ መብዛት የተነሣ በቂ ውኃ ለማግኘት አይችልም፡፡ እስከ ኀሙስ ገበያ ድረስ ለመምጣት የቻለው ውኃም እየተቀዳ ቃጠሎውን ለማጥፋት ለተሰማሩት ወገኖች ነው የተከፋፈለው፡፡ በመሆኑም በዚህም በኩል በጎ አድራጊ አካላትውኃና ውኃ የሚያቀርቡ ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ እንዲራዱ ተጠይቀዋል፡፡

እስከ አሁን - የገዳሙ መነኰሳት እስከ አሁን የተደረገውን ቃጠሎውን የመከላከል ጥረት እንደሚከተለው ገልጸውታል፡- ‹‹በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በምእመኑ ብዛት እሳቱ ጠፍቷል፤ አሁን ባለበት ርቀት  የሚበላውን ያህል በልቶ ስለጨረሰ ከዚህ በኋላ ሊስፋፋ አይችልም፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ መከላከያው፣ ፖሊሱ፣ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ባለሞያዎች ወደ ገዳሙ መዳረሻ በሆኑ መንገዶች አፈሩን እየቆፈሩ ጉድጓዶችን በማውጣት፤ አፈሩን፣ ቅጠሉንና ግንዱን በመከመር ቃጠሎው ወደ ጠበሉ እንዳይገባ አድርገውታል፡፡
አሁን የቃጠሎው ስጋት ያለው ጢሱ በሚታይበት ተራራ ግርጌ፣ በአዱላላ በኩል ጊዳ መሥመር እየተባለ በሚታወቀው አቅጣጫ ነው፡፡ ሌሊት መናንያን ሁኔታውን በንቃት ይጠብቃሉ፡፡ የሚያሰጋ ከሆነ ደወል ይደውላሉ፡፡››
የገዳማውያኑ ምስጋና - ‹‹ለቦታው ተቆርቋሪ ከሆነው ወገን የቀረ ሰው የለም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪው፣ የከተማው ወጣት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ፖሊሱ፣ መከላከያው በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ እዚሁ ነው ያለው፡፡ በተለይ ወጣቱ ለቦታው ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ ሃይላንዳቸውን ብቻ ይዘው ተራራውን ወጥተው ከዚህ መድረሳቸው ብቻ ለእኛ አለኝታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ያስፈጽምላቸው፡፡ ውለታቸው በሰው ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ቦታውን ታድገውታል፡፡››

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

No comments:

Post a Comment